እንኳን ወደ ድረ-ገጻችን
በደኅና መጡ
የኢትዮጵያውያኖች የመረዳጃ እድር በኔዘርላንድስ እ.ኤ.አ. በ2022 የተመሰረተው ኑሮዋቸውን በኔዘርላንድ አገር ባደረጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሲሆን የተመሰረተበትም ዓላማ ኢትዮጵያውያኑ የእድሩ አባል ወይንም የእድር አባል ቤተሰብ ማለትም እድሜው ከ18 አመት በታች የሆነ ልጅ በሞት ሲለይ ለቀብር ስነ ስርዓት ማገዣ ወይም ለአስከሬን ወደ ትውልድ ቦታ መላኪያ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተቋቋመ ነው።
የኢትዮጵያውያኖች የመረዳጃ እድር በኔዘርላንድስ የራሱ የሆነ የመተዳደሪያ ሕገ ደንብ ያለው ሲሆን በኔዘርላንድ የንግድ ምክር ቤት ተመዝግቦ ከህግ የሚጠበቅበትን ግዳጆች አሟልቶ እና አስጠብቆ የሚንቀሳቅስ የኢትዮጵያውያን ማህበረስ የእድሩ አባላት የጋራ ንብረት ነው።
አገልግሎቶቻችን
የእድሩ አባል ለመሆን
የኢትዮጵያኖች የመረዳጃ እድር አባል ለመሆን የሚያስፈልገው በኔዘርላንድስ ውስጥ ነዋሪ የሆነ፣ ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም የእድሩን ሕገ ደንብ የተቀበለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የእድሩ አባል መሆን ይችላል።
የእድሩ አባል ለመሆን የአባልነት መመዝገቢያ የምንጠይቅ ሲሆን የመመዝገቢያው ተመን €100 ነው ይህም በአንዴ የሚከፈል ሲሆን የወራዊ ክፍያው ደግሞ €5 ነው። የወርሃዊ ክፍያውን በየወሩ፣ የወሩ ማገባደጃ ላይ በቀጥታ ዴቢት (automatische incasso) ከባንኮ ላይ ይቆረጣል፣ በአንድ ጊዜ የአመቱን ክፍያ ማድርግም ይቻላል።
በቀጥታ መክፈል ከፍለጉ ከዚህ ወረድ ብሎ በተቀመጠው የባንክ ቁጥር ማስተላለፍ ይችላሉ
Vereniging I.D.I.R Holland
NL35 INGB 0104 0999 84
አባል ለመሆን ከፈለጉ ከእዚህ ግርጌ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው መመዝገቢያ አንቀጹን ይምሉ
ስለ ክፍያ
የቀብር ሥነ ስርዓትን በተመለከት የእድሩ አባል ወይንም ቤተሰቡ በሚፈልገው መንገድ ከእድሩ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ጋር ተወያይቶ የቀብር ሥነ ስረዓቱ እንዲፈጸም የማድረግ መብት አለው።
የወጪውም ተመን በእድሩ መስተዳደሪያ ደንብ "አንቀጽ 2.2.10" መሰረት የተወሰነ ሲሆን ይህ የገንዘብ ተመን የቀብር ዋስትና ያለውም የሌለውም የእድሩ አባል በሞት አደጋ ጊዜ ከእድሩ የሚያገኘው የገንዘብ ተመን አንድ ዓይነት ነው ።
ነገር ግን አንድ አባል በአባልነት ተመዝግቦ ሙሉ ዓመት (12 ወራት) ካልሞላው የገንዘብ ጥቅም አያገኝም።
የግል ሁኔታዎች
ለረጅም ጊዜ የእድሩ አባል ሆነው እና የአባልነት ክፍያዎትን እያሟሉ ኑሮዎትን በሌላ ሃገር ቢያደርጉ ለስራ አስፈጻሚ ቦርድ የኑሮ ሁኔታዎትን አስረድተው አባልነቶትን የመቀጠል መብት ይኖሮታል።
" ሁሉም ስው የቀብር ዋስትና (Uitvaartverzekering) እንዲኖረው እድሩ ይመክራል /ያበረታታል"
ለጥያቄ ወይም ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ። በተቻለ ፍጥነት ጥያቄዎትን ከተሟላ መረጃ ጋር እንልክሎታለን
የዋትስአፕ ወይንም የቴሌግራም መልእክት ለመላክ ከፈለጉ አዶውን ጠቅ ያድርጉ
መደወል ከፍለጉም ከእዚህ ግረጌ ባለው የስልክ ቁጥረ ያገኙናል
0638571383